category
stringclasses
4 values
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
url
stringlengths
36
49
sports
የፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መታገድ ሊመረምር ነው
የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሆነው ዋዳ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መከልከል ዳግም ሊመረምር ነው። ኤጀንሲው ይህን የሚያደርገው አሜሪካዊቷ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪ የካናቢስ ምርመራ ማለፍ ባለመቻሏ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሳትሳተፍ ከቀረች በኋላ ነው። የ21 ዓመቷ ሻካሪ ሪቻርደሰን የወላጅ እናቷን ሞት ተከትሎ ሐዘኗን ለመቋቋም ካናቢስ መጠቀሟን ይፋ አድርጋ ነበር። የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ በካናቢስ ዙሪያ ሳይንሳዊ ምርመራ በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት እንደሚጀመር ገልጾ...
https://www.bbc.com/amharic/news-58571965
politics
ቻይና 'ወኪሏን' ወደ ዩኬ ፓርላማ አስገብታለች መባሉን አስተባበለች
የዩናይትድ ኪንግደም የደህንነት ተቋም (ኤምአይ5) ቻይና ወኪሏን የዩኬ ፓርላማ ውስጥ አስርጋ አስገብታለች ማለቱን ተከትሎ ቤይጂንግ ክሱን አጣጣለች። የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዳለው ክሪስቲን ቺንግ ኩይ የፓርላማ አባላት እና በቀጣይ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር "ግንኙነት እንዲመሠርቱ" አግዛለች ብሏል። ከ420,000 ፓውንድ በላይ ከግለሰቧ ድጋፍ የተደረገለት የሌበር ፓርቲ ተወካዩ ባሪ ጋርዲነርን ጨምሮ ለሌሎች ፖለቲከኞችም ድጋፍ አድርጋለች። መቀመጫውን ለንደን ያደረገው...
https://www.bbc.com/amharic/59991402
sports
በኢትዮጵያና ታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ግጥሚያ የተከሰተው ምንድን ነው?
ኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የታንዛኒያ አቻዋን 2 ለ1 ረትታለች። የዚህ ጨዋታ ማብቂያ ግን እንደ ሌሎች ግጥሚያዎች ተጫዋቾች ተጨባብጠው የተለያዩበት አይደለም። ለመሆኑ የተፈጠረው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ሰኞ ዕለት ባደረገችው የመጀመሪያው ጨዋታዋ ጅቡቲን 7 ለምንም መርታቷ ይታወሳል። ቀጣይ ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር ግጥሚያ የነበራት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 5 ለባዶ አሸንፋለች። ሶስተኛው የኢትዮጵያ ጨዋታ ከታንዛኒያ ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59161580
sports
ለ39 ዓመታት እራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አረፈ
ላለፉት 39 ዓመታት ኮማ ውስጥ የነበረው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ዣን ፒየር አዳምስ በ73 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሆስፒታል የገባው እአአ ግንቦት 1982 ለጉልበት ቀዶ ሕክምና ነበር። ማደንዘዣ ሲሰጠው በተፈጠረ ስህተት ምክንያት እራሱን ከሳተ በኋላ ለ39 ዓመታት ከኮማ አልነቃም። ሴኔጋል የተወለደው አጥቂው ዣን ፒየር፤ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና ኒይስ ቡድን ከ140 ጊዜ በላይ ተሰልፏል። ፓሪስ ሴንት ዠርመን (ፒኤስጂ) ባወጣው መግለጫ፤ "ግርማ ሞገስ ያለው፣ ልምድ ...
https://www.bbc.com/amharic/news-58468255
politics
የጀርሲ ፍርድ ቤት የሮማን አብራሞቪችን 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረቶች አገደ
ከሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች ጋር የተያያዙ እና 7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ንብረቶች በጀርሲ ፍርድ ቤት ታግደዋል። ከቀናት በፊት የጀርሲ ፖሊስ በደሴቲቱ ላይ ከባለሀሃብቱ አብራሞቪች የንግድ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ በተጠረጠሩ ቦታዎች ፈተሻ ማድረጉን የጀርሲ የህግ መኮንኖች ጽህፈት ቤት አሳውቋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ቢሊየነሩ አብራሞቪች በዩኬ ማዕቀብ ውስጥ ከተካተቱበት ውስጥ ይገኛሉ። የደሴቲቱ ሀገር ጀርሲ የዩኬን በመከተል በተመሳሳይ ሰዎች ላይ ማዕቀ...
https://www.bbc.com/amharic/news-61103519
sports
ጉዬ አዶሎ፡ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር በመወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል"
የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ጉዬ አዶላ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር መወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል" ሲል ተናገረ። አትሌት ጉዬ ውድድሩ እንደ አጠቃላይ ቆንጆ ነበር ያለ ካለ በኋላ፤ "በሰዓቱ ደስተኛ ባልሆነም አንደኛ በመውጣቴ ደስ ብሎኛል" ብሏል። በውድድሩ ጥሩ ሰዓት ያልተመዘገበው በበርሊን የነበረው ከፍተኛ ሙቀት እንደምክንያት ያነሳው አትሌቱ፤ በውድድር ላይ የሚያጋጥሙ ስህተቶችን በማራም በቀጣይ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። "የማስበው የኤሊዩድ ሪኮርድ መስበር ነው...
https://www.bbc.com/amharic/news-58704717
politics
የአዲስ ዓመት ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት እንዲሆን ነው
የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በመስከረም ወር 2005 ዓ. ም. ነበር የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ኢትዮጵያን እንዲመሩ የተሾሙት። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደርነትን ጨምሮ በበርካታ የክልል ብሎም የፌደራል የሥራ ኃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቦርድ አመራርነት ያገለግላሉ። እንዲሁም ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cl5845y7v53o
health
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ
በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። "ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59515396
sports
አሜሪካ አበረታች መድኃኒት የሚጠቀሙ ስፖርተኞችን በወንጀል ልትከስ ነው
የአሜሪካ ምክር ቤት ሴኔት በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ የአበረታች መድኃኒት የተጠቀመ ማንኛውንም ሰው የወንጀል ክስ እንዲመሰረትበት የሚያስችልን ረቂቅ ህግ አፀደቀ። የአበረታች መድኃኒት ጥሰቶችን ባጋለጠው በሩሲያዊው ግሪጎሪ ሮድቼንኮቭ ስም የሮድቼንኮቭ ፀረ-አበረታች አዋጅ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲፈርሙበት ሕግ ይሆናል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ትራቪስ ታይጋርት ውሳኔውን “ንፁህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ትግል ትልቅ” ነው ሲሉ ገል...
https://www.bbc.com/amharic/news-54978864
politics
የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ ቢያንስ ሦስት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ በርካቶች ለጉዳት ተዳረጉ
በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተቃውመው አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ወታደሮች በተኮሱት ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 80 የሚሆኑ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው ተዘገበ። ተቃዋሚዎቹ አደባባይ የወጡት ወታደራዊ ኃይሉ የሲቪል አስተዳደሩን ከበተነ፣ የፖለቲካ መሪዎችን ካሰረ እና በአገሪቷ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ ነው። ወታደሮች የተቃውሞውን አስተባባሪዎች ለመያዝ በዋና መዲናዋ ካርቱም የቤት ለቤት አሰሳ እያደረጉ እንደሆነም ተነግሯል። በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በዓለም ዙሪያ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59042602
sports
ኢትዮጵያውያኑ የሴቶችና የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ውድድር ክብረ ወሰንን ሰበሩ
ኢትዮጵያውያኑ እጅጋየሁ ታዬ እና በሪሁ አረጋዊ የዓለም የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ክብረ ወሰን መስበራቸውን የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል አስታወቀ። ትናንት አርብ በፈረንጆቹ አቆጣጠር የዓመቱ የመጨረሻ ዕለት በአውሮፓዊቷ ስፔን ባርሴሎና ከተማ በኩርሳ ዴልስ ናሶስ በተካሄደ ውድድር ነው ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ክብረ ወሰን የሰበሩት። በሴቶቹ እጅጋየሁ ታዬ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ እንዲሁም በወንዶቹ በሪሁ አረጋዊ በ12 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በማጣናቀቅ ነው ቀደም ሲል በርቀቱ የተያዙትን ክብረ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59845516
sports
ለኢትዮጵያውያንና ለአፍሪካውያን ፈር ቀዳጅ ድል ያስመዘገበችው ፋጡማ ሮባ
ፋጡማ ሮባ የመጀመሪያውን የሴቶች ማራቶን ፈር ቀዳጅ ድሏን እ.ኤ.አ. በ1996 በሞሮኮ ማራክሽ ነበር የተቀዳጀችው። በመቀጠልም ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን አሸናፊ ሆነች። ከሮም አሸናፊነት በኋላም በ1996 በአትላንታ አሜሪካ በሚደረገው የኦሊምፒክ ውድድር በ2:26:05 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች። በወቅቱ ፋጡማን በመከተል ሁለት ደቂቃ ዘግይተው የሩሲያዋ ቫለንቲና ይጎሮቫና ጃፓናዊቷ ዩኩ አርሞሪ 2ኛና 3ኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል። ከ1997 እስከ 1999 የተካሄዱ የቦስተን ማራቶን ...
https://www.bbc.com/amharic/news-56156447
politics
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሦስት የተቃዋሚ አባላትን በካቢኔያቸው ውስጥ አካተቱ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በሚኒስተርነት እንዲያገለግሉ ለሕዝብ ተወካዮች አቅርበው አስሹመዋል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ በሚኒስትር ተሹመዋል። ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ በለጠ ሞላ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ እንዲሁም...
https://www.bbc.com/amharic/58814095
business
የዩክሬኑ ጦርነት ባለፉት 50 ዓመታት ያልታየ የዋጋ ንረት እንደሚያስከትል ተገለጸ
የዩክሬን ጦርነት ከአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ወዲህ በዓለማችን ታይቶ የማይታወቅ የሸቀጦች እጥረት ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ባንክ አሳስቧል። የዓለም ባንክ ባወጣው ትንበያ መሠረት የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በበርካታ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያስከተለ ሲሆን ከነዚህ መካከል በዋነኛነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ስንዴ እንዲሁም ጥጥ ይገኙበታል። "የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ጫናዎችን እያስከተለ ነው" ብለዋል ሪፖርቱን ካዘጋጁት መካከል አንደኛው የሆኑት ፒተር ኔግል። አክለውም "በመላው ዓለም የ...
https://www.bbc.com/amharic/61240082
sports
ዛየን አሊ ሰልማን፡ በአርሰናል የእግር ኳስ ቡድን የተመለመለው የአራት ዓመቱ ታዳጊ
ዛየን አሊ ሰልማን የእንግሊዝ ትልቅ የእግር ኳስ ቡድንን ቀልብ ሲስብ ዕድሜው ገና አራት ነበር። ዛየን ያለው ችሎታ ከእድሜው በሁለት እጥፍ የላቀ ነው ሲሉ ይናገራሉ፤ አሰልጣኞቹ። የአርሰናል ቅድመ መደበኛ አካዳሚ እያሰለጠነው የሚገኘው ዛየን ገና ከአሁኑ ከሌሎች ስመ ገናና የእግር ኳስ ቡድኖች ጥሪ እየቀረበለት ይገናል።
https://www.bbc.com/amharic/59047067
sports
ሴቶች ስታዲየም እንዲገቡ በቅርቡ የፈቀደችው ሳዑዲ የሴቶች ሊግን ልታስጀምር ነው
ሴቶች ስታዲየም ገብትው ኳስ እንዳይመለከቱ ትከለክል የነበረችው ሳዑዲ አራቢያ የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ልታስጀምር ነው። በሊጉ የሚሳተፉ ቡድኖች በመዲናዋ ሪያድ እና በሌሎች ሁለት ከተሞች ውድድሮችን ያካሂዳሉ። አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን በሳዑዲ እያካሄዱ ካለው የለውጥ እርምጃ መካከል ይህ ውሳኔ ተጠቃሽ ነው። የሰብዓ መብት ተሟጋቾች ግን አሁንም በሳዑዲ የሴቶች መብት ላይ ገደብ ተጥሏል ይላሉ። ባለስልጣናት የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ማቋቋም ያስፈለገው ሴቶች በስፖርት ያላቸው ተሳትፎ ለማሳዳግ ነው ...
https://www.bbc.com/amharic/news-51641657
sports
ተጠባቂውን የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ማን በበላይነት ያጠናቅቃል?
በዚህ ሳምንትስ ከሊቨርፑል እና ከማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል? “ወደ ኤሚሬትስ ስታዲም ከማቅናታቸው በፊት ሊቨርፑሎች ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ይመለሳሉ በሚል ግምቴን ስሰጣቸው ቆይቻለሁ” ይላል ሱቶን። “ግን አልተሳካም። በቻምፒዮንስ ሊግ ሬንጀርስን 7 ለ 1 ማሸነፍ ቢችሉም ከፊታቸውን ከባድ ጨዋታ አለ።” ሱቶን ይህንን ጨዋታ ጨምሮ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን ውድድር ዓመቱን በድንቅ መንገድ የጀመሩት ብሬንትፎርዶች ከሰሞኑ ውጤት አልቀናቸውም። ባለፈው ሳምንት በኒውካ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72d77v22xwo
business
ትግራይ ውስጥ በረሃብ ሳቢያ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ
በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ ክልል ሰዎች እና እንስሳት በረሃብ እና በመሠረታዊ የህክምና እንክብካቤ እጥረት እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ግብርና ኃላፊ ገለጹ። "በመንደሮች እና በከተሞች ውስጥ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት አለ። እናም በክልሉ ውሰጥ እየተከሰተ ያለው ቀውስ እኛ ከምናውቀው የበለጠ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል። ህወሓትም ባወጣው መግለጫ ላይ የክልሉን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ በነሐሴ ወር 150 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተመዝግቧል ...
https://www.bbc.com/amharic/news-58472069
sports
ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት በርካታ የውጭ አገር ሠራተኞች የሞቱባት ኳታር የሠራተኞች አያያዝ
በጉጉት የሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ ውድድሮች እሁድ ኅዳር 11/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከተለያየ የዓለማችን ክፍሎች የሚተሙ የእግር ኳስ ደጋፊዎችም በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ስደተኛ ሠራተኞች አማካኝነት በተገነቡ ስታዲየሞች ጨዋታዎችን ይመለከታሉ። በሠራተኞች ላይ ሞትን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች ደርሰዋል በሚልም ኳታር ተደራራቢ ውግዘቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኳታር ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሰባት ስታዲየሞችን እንዲሁም አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ በርካታ መንገዶችን የሚያገናኝ መስመር እና 1...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cj594vzzzj5o
sports
ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ በነበረው ጨዋታ የተፈጠሩ ክስተቶች እንዲመረመሩ ጠየቀ
ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲዘገይ ያደረገውና ደጋፊዎች ያጋጠሟቸው "ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች" ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት የደህንንት ምክንያቶችን ጠቅሶ ጨዋታውን እንዲዘገይ ያደረገው ሲሆን በዚህም ጨዋታው ከ30 ደቂቃ በላይ መዘግየት አጋጥሞታል። በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም የተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ እስከ ምሽቱ አራት ተኩል ድረስ ያልተጀመረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ሪያል ...
https://www.bbc.com/amharic/news-61612597
politics
በሶማሊያ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ማን ናቸው?
የመሪነት ሥልጣንን ሲጨብጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እአአ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ ግን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ረቷቸው። በቀውስ በምትናጠው የአፍሪካ ቀንድ አገር ሶማሊያ በድጋሚ በመመረጥ ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ታሪክ ሠርተዋል። የትላንቱ ምርጫ በአገሪቷ ታሪክ ፉክክር የበዛበት ነበር። የምርጫ ሂደቱ በሦስት ዙር ተካሂዷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት በትምህርት ዘርፍ ይታወቃሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ማጠንጠኛ ሶማሊያን ከተቀረው ዓለ...
https://www.bbc.com/amharic/news-61468546
health
በአውስትራሊያ በአፍንጫ የሚወሰድ የኮቪድ-19 መከላከያ ላይ ሙከራ እየተደረገ ነው
የደም መርጋት ሲያጋጥም ጥቅም ላይ የሚውለው መድኃኒት (blood thinner) ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እንዲውል የአውስትራሊያ አጥኚዎች ምርምር እያደረጉበት ይገኛሉ። ሙከራ የተደረገበት መድኃኒት በአፍንጫ የሚሳብ (nasal spray) ነው። አጥኚዎቹ እንዳሉት፤ መድኃኒቱ የኮሮናቫይረስ የፕሮቲን መጠን እንዳይጨምር በማድረግ የበሽታውን ስርጭት ይከላከላል ተብሎ ይታመናል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአፍንጫቸው መድኃኒቱን ሲወስዱ በሽታውን ማስተላለፍ ማቆማቸውን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። ሙከራው እአአ በ2022...
https://www.bbc.com/amharic/news-59770888
sports
የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በስፖርቱ ውስጥ ጾታዊ ጥቃት መኖሩን ተናገሩ
የቀድሞዋ የአውስትራሊያ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋች ሊሳ ዴ ቫና በስፖርቱ ውስጥ ስላለው የጾታዊ ጥቃት ባህል ለአንድ ጋዜጣ የሰጠችው ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ሆኗል። የ36 ዓመቷ የቀድሞ የማቲልዳስ የእግር ኳስ ቡድን አጥቂ በይፋ መናገሯን ተከትሎም ሌሎች የሃገሪቱ ሴት ተጫዋቾች ተመሳሳይ ሃሳቦችን ማንጸባረቅ ጀምረዋል። የአውስትራሊያ የእግር ኳስ ባለስልጣን እንዲህ ያሉ ቅሬታዎች ቀርበውለት እንደማያውቁ በመግለጽ እነዚህን ክሶች ተከትሎ ግን ሊሳን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾች የሚያሰሙትን አቤቱታ ተቀብሎ ገለልተኛ አጣሪ...
https://www.bbc.com/amharic/58814088
business
ኮሮና ቫይረስ፡ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚያዊ ድቀት እንደሚያጋጥማቸው ተነበየ
የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተነበየ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በ52 የአፍሪካ አገሮች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላ አህጉሪቱ 10,250 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችም ቁጥርም 492 ደር...
https://www.bbc.com/amharic/news-52230764
health
ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ?
እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59596054
politics
የሚየንማር ዜጎች ሥራ አቁመው ተቃውሞውን ተቀላቀሉ
በሚየንማር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት አን ሳን ሱ ቺ እንዲለቀቁ የሚጠይቀው አገራዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። ሠራተኞችም የሥራ ማቆም አድማ በመምታት ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመዲናዋ ፒ ታው በሚገኙት ያንጎን እና ማንዳሊ አደባባዮች ተቃውሞ እያካሄዱ ነው። ሚየንማር እንደዚህ ያለ ተቃውሞ ካየች ከአስር ዓመት በላይ ይሆኗታል። ወታደራዊ ሃይሉ የሚየንማርን መሪ በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ለአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። መሪዋ፣ ፕሬዘዳንት ዊን ሚንት እ...
https://www.bbc.com/amharic/55976538
health
በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት ጨመረ
በአፍሪካ በሕይወት የመቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። አፍሪካ ውስጥ ሰዎች በሕይወት ይቆዩበት የነበረው አማካይ ዕድሜ ከዚህ ቀደም 46 የነበረ ሲሆን፣ አሁን ወደ 56 ከፍ ብሏል። ሰዎች ዘለግ ያሉ ዓመታት መኖር የጀመሩት የተሻለ የሕክምና አቅርቦት በመዘርጋቱ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ነገር ግን የዕድሜ ልኬቱ ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር አሁንም ከአማካዩ ያነሰ እንደሆነ አክሏል። ሰዎች በሕይወት የሚቆዩበት ዕድሜ የሚሰላው ዕድሜያቸውን፣ ጾታቸውን እና የሚኖሩ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cml9zd8vngmo
health
ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው?
ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መከተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55745103
health
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት በኮቪድ ተያዙ
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ኮቪድ ተመርምረው ተህዋሲው እንደተገኘባቸው ይፋ አደረጉ። የ67 ዓመቱ ፕሬዝዳንት በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት አሁን የበሽታውን ቀላል ምልክቶችን ማሳየት ጀምረዋል። የፕሬዝዳንቱ በተህዋሲው የመያዝ ዜና የመጣው ሜክሲኮ በወረርሽኝ እየታመሰች ባለችበት ወቅት ነው። ሜክሲኮ እስከዛሬ ከ150ሺህ ባላይ ዜጎቿን በተህዋሲው አጥታለች። ሎፔዝ ኦብራዶር አገሪቱን ከቤቴ ሆኜ መምራቴን እቀጥላለሁ ብለዋል። ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ለማግኘትም ከፑቲን ጋር እነጋገራለሁ ብለ...
https://www.bbc.com/amharic/55792459
health
በፈረንሳይ የፌስቡክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲያጥላሉ ገንዘብ ቀረበላቸው
በፈረንሳይ ማንነቱ ያልታወቀ አንድ አካል በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን እያደነ የኮቪድ-19 ክትባትን ካጥላላችሁልኝ ከፍተኛ ገንዘብ እሰጣችኋለሁ እያለ በማባበል ላይ ነው፡፡ ደለብ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው ያመኑ በርካታ የፌስቡክ፣ የዩትዩብና የኢኒስታግራም ዝነኞች ጉዳዩን አደባባይ አውጥተውታል፡፡ ማንነቱ ያልታወቀው ይህ ገንዘብ ከፋይ አካል/ድርጅት መቀመጫውን በዩኬ እንዳደረገ ቢገመትም ሊደረስበት ግን አልቻለም፡፡ ዝነኞቹን በገንዘብ የሚያማልለው ኢሜይል እየላከ ሲሆን በተለ...
https://www.bbc.com/amharic/57251178
health
ወረርሽኙ መቀጠሉ የዙምን ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በርካታ የአለማችን ህዝብ በቤት መገደቡ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ለስብሰባዎችና ለሌሎች ዝግጅቶች መገልገያ የሆነው የድምፅና የቪዲዮው መተግበሪያው ዙም ከፍተኛ ሽያጭ እንዳስመዘገበና ትርፉም በዚሁም ሊቀጥልም እንደሚችል ኩባንያው አስታውቋል። በካሊፎርኒያ መቀመጫውን ያደረገው የዙም ኩባንያ 2.5 ቢሊዮን ዶላርም ትርፍ አገኛለሁ ብሎ የተነበየ ሲሆን ይህም በመጋቢት ወር አገኘዋለሁ ብሎ ካሰበው እጥፍ ነው ተብሏል። ወረርሽኙን ተከትሎም ስሙ የገነነው ዙም አገራት ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝን በ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55141283
sports
ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀውበት ያለፈው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን
በአሜሪካዋ ግዛት ኦሪገን፣ ዩጂን ከተማ ውስጥ ሲካሄድ በሰነበተው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ሴት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታሪክ በማስመዝገብ ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ካስመዘገበቻቸው 10 ሜዳሊያዎች 7ቱ የተመዘገቡት በተለያዩ ርቀቶች በተሳተፉ ሴት አትሌቶች አማካይነት የተገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ በ4 የወርቅ፣ በ4 የብር እና በ2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም የአትሌቲ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyep9eld3deo
sports
በአንድ ቀን የተወለዱ ልጆች በስሟ እንዲጠሩ ስለተደረገላት አትሌት ያውቃሉ?
ናዋል ኤል ሞውታዋኬል ሞሮኳዊት አትሌት ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 8፣ 1984 በሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ድል ተቀዳጅታለች። ማሸነፏ እጅግ ያስደሰታቸው ሞሮኳዊው ንጉሥ ሐሰን በእለቱ የተወለዱ ሴቶች ባጠቃላይ ናዋል ተብለው እንዲጠሩ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ሰሞኑን 36ኛ ዓመት ልደታቸውን የሚያከብሩ የሞሮኮ ሴቶች ስማቸው ናዋል የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ናዋል በኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ሞሮኳዊት ናት። በ400 ሜትር የመሰናክል ዝላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሴትም ናት። በሎስ አ...
https://www.bbc.com/amharic/news-53740809
politics
በጣሊያን ኤምባሲ የሚገኙ የቀድሞ ባለስልጣናት በቀናት ውስጥ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ
ሠላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የሚገኙት ሁለት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት ይቅርታ ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ። እነዚህ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ላለፉት ሦሰት አስርት ዓመታት ቆይተዋል። የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባን ከመያዙ አንድ ቀን ቀደም ብለው በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ከተጠለሉት አራት የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣንት መካከል የ...
https://www.bbc.com/amharic/55314978
business
በፈረንሳይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ 874 መኪናዎች ተቃጠሉ
ፈረንሳይ ውስጥ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአጠቃላይ 874 መኪናዎች ዶግ አመድ መሆናቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ቢሆንም የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ይህ ቁጥር ከ2019 ጋር ሲነፃፀር የወረደ ነው። ባለሥልጣናቱ ጨምረው እንደጠቆሙት በዘንድሮው የአዲስ ዓመት በርካታ ሰዎች ለጥቂት ሰዓታት በሕግ ጥላ ሥር እንዲቆዩ ተደርገዋል። ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል የተጣለውን ሰዓት እላፊ ተከትሎ ፈረንሳይ ምንም ዓይነት ረብሻ አላስተናገደችም። ከፈረንጆቹ 2005 ጀምሮ መኪና ማቃጠል ፈረንሳይ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59850637
business
የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ያለሙት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች
በተለያዩ ምክንያቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች የመሠረታዊ ምርቶች ዋጋ ያለማቋረጥ እያሻቀበ ዜጎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። ለዋጋ ግሽበቱ ምክንያት በመሆን ከሚጠቀሱት መካከል በአገሪቱ ያለው ጦርነት እና ያስከተላቸው ጊዜያዊ ችግሮች እንዲሁም በወጪ ንግድ ያለው መዛነፍ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ እና በሌሎች ዓለም አቀፋዊ የምጣኔ ሀብት ምክንያቶች በኢትዮጵያ ኑሮ 'የማይቀመሰ' ሆኗል የሚለውን ብዙዎች የሚጋሩት ነው። ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59839436
health
ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ
ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ...
https://www.bbc.com/amharic/news-54423275
health
ለሁለተኛ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዘው ከመጀመሪያው በባሰ በጠና ታመመ
አሜሪካ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው፤ ከመጀመሪያው በባሰ ሁኔታ በጠና መታመሙን ሐኪሞች ተናገሩ። የ25 ዓመቱ ግለሰብ ከሳምባው በቂ ኦክስጅን ወደ ሰውነቱ መዘዋወር ስላልቻለ ሆስፒታል ገብቷል። በድጋሚ በቫይረሱ የመያዝ እድል አነስተኛ ሲሆን፤ ግለሰቡም እያገገመ ይገኛል። የኔቫዳ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በተለየ ሁኔታ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሚያደርገው ህመም ወይም በሽታ የመቋቋም ኃይል ውስንንነት የለበትም። ግለሰቡ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ድረስ ያሳየው የበሽታው ምልክቶች ቀጣዮቹ ናቸው፦ ሳይን...
https://www.bbc.com/amharic/news-54527534
sports
ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ወሰኑ
የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ክለቡን ለመሸጥ ማቀዳቸውን ገለጹ። ባለሃብቱ አብራሞቪች በፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ድረ-ገጽ ላይ ባወጡት መግለጫ "በጣም ከባዱን እና የሚያመውን ውሳኔ" መወሰናቸውን ተናግረዋል። ሩሲያዊው "ምንም ዓይነት ብድር እንዲመለስ" ያልጠየቁ ሲሆን የሽያጩ ገቢም ለጦርነት ተጎጂዎች ይውላል ብለዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ በኋላ አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት እንዳስታወቁት የቼልሲን "ኃላፊነት እና ተጠሪነት" ለፋውንዴሽኑ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። ይህም ክለቡን ከ 1.5 ቢሊየ...
https://www.bbc.com/amharic/news-60596117
sports
እግር ኳስ፡ ህይወቱ በሱስ ምክንያት የተመሳቀለው የፕሪምየር ሊግ ቡድን አምበል
"በጣም ብዙ እርዳታ አስፈልጎኝ ነበር። ወደ ሌላ አይነት ሕይወት ለመሸጋገር ከብዶኝ ነበር፤ ምክንያቱም ህይወቴን በሙሉ እግር ኳስን ብቻ ነበር የማውቀው። ከእንደዚያ አይነት ቦታ መውደቅ ከባድ ነው።" ክላውስ ሉንደክቫም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በአውሮፓውያኑ 2008 ከእግር ኳስ እራሱን እንዲያገል መገደዱን በተመለከተ የተናገረው ነው። ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ደግሞ የአልኮልና የአደንዛኝ እጽ ሱሰኛ ሆነ። ክላውስ በወቅቱ የ35 ዓመት እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55287481
health
ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ
በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳ...
https://www.bbc.com/amharic/53640749
sports
በካሜሮን ዕድሜያቸውን ያጭበረበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች ሊቀጡ ነው
በካሜሮን ዕድሜያቸውን አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ አርባ አራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። ተጫዋቾቹ ከዕድሜያቸው በተጨማሪ ማንነታቸውንም አጭበርብረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማተር ክለቦች የተውጣጡ ሲሆን ጥቂቶቹ ደግሞ የብሄራዊ ሊጎች ተጫዋቾች መሆናቸውን የካሜሮን እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፌካፉት አስታውቋል። ተጫዋቾቹ በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ለስድስት ወር ያህል ከየትኛውም ጨዋታ የመታገድ  ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የፌካፉት ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cl7gxeyvdggo
health
አስትራዜኒካ የደም መርጋት ያስከትላል? የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን ሊገመግም ነው
የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ እየተወራበት ያለውን የኦክስፎርድ አስትራዜኒካን ውጤታማነትን በተለይም ከደም መርጋት ጋር ያለውን ተያያዥነት በክትባት ሊቃውንት ሊያስገመግም ነው፡፡ ክትባቱ ውጤታማ ነው ከተባለ በኋላ ብዙ አገራት ለሕዝባቸው ማደል ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ብዙ የአውሮፓ አገራት ለጊዜው የክትባት እደላው እንዲቆም ወስነዋል፡፡ አንዳንድ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ደማቸው የመርጋት ምልክት በማሳየቱ ነው ስጋት የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የክትባት ሊቃውንት ለ...
https://www.bbc.com/amharic/news-56411449
business
የጓቲማላ ተቃዋሚዎች ምክር ቤቱን በእሳት አቃጠሉ
በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓቲማላውያን ተቃዋሚዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ህንፃ መዝብረው እሳት ለቀውበታል ተብሏል። ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል። የተወሰነው የህንፃው ክፍልም በቃጠሎው ጉዳት ደርሶበታል። የእሳት አደጋ አገልግሎት ሰራተኞች እሳቱን ማጥፋት ቢችሉም በርካታ ሰዎችም በጭሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ህክምናም እየተደረገላቸውይገኛሉ። ከሰሞኑ ምክር ቤቱ ያፀደቀውን በጀት በመቃወምም ነው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉት። በጀቱ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55033851
health
ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ ያልተነገረለት ኮቪድ-19 በአንጎላችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ምንድን ነው?
ስትሮክ፣ ቅዠት፣ ጭንቀት፣ ግራ መጋባት፣ ድካም ፣ እያለ ይቀጥላል። ኮቪድ-19 የመተንፈሻ አካላት ላይ ብቻ ጉዳት የሚያደርስ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። እያንዳንዱ ሳምንት ባለፈ ቁጥር ኮሮናቫይረስ ዘርፈ ብዙ አእምሯዊና አካላዊ ጉዳቶችን ማስከተል ይጀምራል። ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡ በርካታ ሰዎች በመጀመሪያ አካባቢ ብዙም የሚሰጋ ህመም የማይሰማቸው ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ማስታወስ አለመቻልና ድካምን የመሳሰሉ ጠንከር ያሉ ምልክቶች ማሳየት ይጀምራሉ። ፖል ማይልሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሁለት ከባ...
https://www.bbc.com/amharic/news-53282426
sports
ፊፋ በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት መመርመር ጀመረ
እንግሊዝ ሃንጋሪን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ በተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን የዘረኝነት ጥቃት ለመመርመር ፊፋ ሥራ መጀመሩ ተነገረ። ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ውስጥ በተካሄደው የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ የእንግሊዝ ተጫዋቾቹ ራሂም ስተርሊንግ እና ጁድ ቤሊንግሃም የዘረኝነት ጥቃት ኢላማ ሆነው ነበር። ቡዳፔስት ውስጥ በሚገኘው ፑስካስ አሬና ስታዲየም በተደረገውና እንግሊዝ በሰፊ የግብ ልዩነት ባሸነፈችበት ጨዋታ ወቅት ተጨዋቾቹ ላይ የተለያዩ ነገሮች ከተመልካቾቹ ተወርውሮባቸዋል።...
https://www.bbc.com/amharic/news-58386459
politics
ክልልነት በጠየቁ የደቡብ አካባቢዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ስር ያሉ 6 ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ክልል እንሁን ጥያቄ ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም. ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ በ1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በአንድ ክልል እንጠቃለል ጥያቄ ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላልፏል። በዚህም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች፣ እንዲሁም ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0v4j8l3yqyo
health
ኮሮናቫይረስ፡ በቱርክ የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ የኮሮና ህሙማንን ገደለ
በቱርክ በሚገኝ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ማዕከል የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ ዘጠኝ የኮሮና ህሙማንን ገድሏል። አደጋው ያጋጠመው ጋዚንቴፕ በምትባለው ግዛት የሚገኘው የሳንኮ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ነው። የቬንትሌተሩም መፈንዳትም በፅኑ ህሙማኑ ክፍል ውስጥ እሳት ማስነሳቱንም የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። አንደኛው ህመምተኛም ወደ ሌላ ሆስፒታል ሊዛወር ሲል ነው የሞተው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ 2 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን 17 ሺህ 610 ሰዎችም ህይወታቸው...
https://www.bbc.com/amharic/news-55383518
health
ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች
ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። "በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ" ነበር ብለዋል...
https://www.bbc.com/amharic/news-56073530
health
ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ
የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚ...
https://www.bbc.com/amharic/news-53627157
sports
ዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች፡ ፈረንሳይ ድል ሲቀናት አርጀንቲና እጅ ሰጥታለች
የአምናዋ የዓለም ሻምፒዮና ፈረንሳይ ከመመራት ተነስታ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አውስትራሊያን በማሸነፍ አጀማመሯን አሳምራለች። ፈረንሳይ እንደካሪም ቤንዜማ፣ ንጎሎ ካንቴ እና ፖል ፖግባ ያሉ ኮከቦቿን በጉዳት አጥታ ነው ወደ ዓለም ዋንጫው ያቀናችው። ትላንት በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታዋ በአውስትራሊያ ቀድሞ ጎል ተቆጥሮባታል። ክሬግ ጉድዊን ነው ጎሏን ለቢጫ ለባሾቹ ያስቆጠረው። አድሪዬ ራቢዮ ሰማያዊዎቹን በ27ኛው ደቂቃ አቻ አደረገ። ኦሊቨር ዥሩ ሁለተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ፈረንሳይ 2 ለ 0 በምምራት ወደ ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0491jyxz8o
sports
አሠልጣኝ ኤሪክሰንን ጨምሮ ታዋቂ ተጫዋቾችን ያጭበረበረው ደላላ
ለእግር ኳስ ደጋፊዎች እንደ መጀመሪያዋ የውድድር ዘመን ጨዋታ ጣፋጭ የለም። በጉጉት የጠበቁት ሊግ አሊያም የዋንጫ ፍልሚያ ሲጀምር የምትታየው የመጀመሪያዋ ጨዋታ እንደ ጨቅላ የሚያስቦርቅ ነገር አላት። ጊዜው 2009 በፈረንጆቹ። በእንግሊዝ ሊግ ሁለት የሚጫወተው ኖትስ ካውንቲ የ09/10 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ጨዋታውን እያካሄደ ነው። ኖትስ ካውንቲ ከዚህ ጨዋታ አንድ ወር ቀድሞ ሙንቶ ፋይናንስ በሚባል ጥምር ተቋም ተገዝቷል። ሙንቶ፤ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኖትስ ካውንቲን ከፕሪሚዬር ሊጉ ዝቅ ብሎ ለ...
https://www.bbc.com/amharic/news-61037984
politics
በምሥራቅ ወለጋ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው እስረኞችን ማስመለጣቸው ተነገረ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስመልጠው በርካታ የፖሊስ አባላትን ማቁሰላቸው ተነገረ። ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው ጥቃቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ዕለት ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቢቢሲ ጥያቄያ ቢቀርብላቸውም አስካሁን ያሉት ነገር የለም። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራውና ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ...
https://www.bbc.com/amharic/news-58424823
sports
95 ለ 0 እና 91 ለ 1 የተጠናቀቁ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ
የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 በተጠናቀቁ ሁለት የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ። የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ጨዋታዎች ሊታመን የማይችል 187 ጎሎች መቆጠራቸውን ‘አሳፋሪ’ ብሎታል። በሴራ ሊዮን በሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ሊግ በተደረጉት ግጥሚያዎች ካሁንላ ሬንጀርስ እና ገልፍ ኮኖ ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን በከፍተኛ የጎል ብልጫ አሸንፈዋል። ካሁንላ ክለብ ሉምቤቡ ዩናይትድ የተሰኘውን ቡድን 95 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን፤ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪየም ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4pjl34k13o
business
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ
የኬንያው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መስከረም 26/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ። ኩባንያው በነሐሴ ወር ከአዲስ አበባ በ500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የድሬዳዋ ከተማ ነበር የሙከራ አገልግሎቱን የጀመረው። በቀጣይ በነበሩ ሳምንታት ደግሞ በአስር ከተሞች ማለትም በሐረር፣ በሐረማያ፣ በአዳማ፣ በባሕር ዳር፣ በቢሾፍቱ፣ በደብረ ብርሃን፣ በጎንደር እና በሌሎች ከተሞች የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ከእነዚህ ሙከራዎች በኋላ ዛሬ በይፋ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2p31gzlryo
health
ኮሮናቫይረስ ፡ ወደ ታይዋን ኮቪድ-19 ቫይረስ አስገብቷል የተባለው አብራሪ ከሥራ ተባረረ
የኮሮናቫይረስን ወደ ታይዋን ይዞ ገብቷል የባለ ኒው ዚላንዳዊው የአውሮፕላን አብራሪ ከሥራ ተሰናብቷል። ሰውዬው ታይዋን ውስጥ ከወራት በኋላ ለተከሰተው የኮሮናቫይረስ የማኅበረሰብ ሥርጭት ተጠያቂ ነው ተብሎ ነው ከሥራው የተባረረው። አብራሪው ኢቫ ኤይር ለተሰኘው የታይዋን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ባለፈው ማክሰኞ ከአብራሪው ጋር ግንኙነት የነበረው ግለሰብ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጿል። ታይዋን ለ253 ቀናት አንድም በአገር ውስጥ ያለ ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘባትም ነበር። ይህ ዜና ከተሰ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55435035
politics
"ባሌን በብርሃን ፍጥነት ነው የገደሉት" የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት
በቅርቡ የተገደሉት የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት ገዳዮች ወደቤታቸው መጥተው ባላቸውን በእኩለ ለሊት ሲገድሉባቸው የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ማርቲን ሞይዝ እንዳሉት ጥቃቱ በጣም በፍጥነት የተፈፀመ ከመሆኑ የተነሳ ባላቸው ጆቨኔል "አንድም ቃል መተንፈስ" አልቻሉም። ፕሬዝደንት ሞይዝ ባፈለው ረቡዕ ነው የተገደሉት። ገዳዮች ተብለው የተጠረጠሩት ደግሞ 28 የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። ሚስታቸው ማርቲን ሞይዝ ተጎድተው በአሜሪካዋ ከተማ ማያሚ ሕክምና ሲያገኙ ቆይተው አሁን አገግመዋል። ቅዳሜ ዕለት በትዊተር ገፃቸው...
https://www.bbc.com/amharic/news-57794473
business
ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ በክሪፕቶከረንሲ ያጭበረበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በክሪፕቶከረንሲ አማካይነት 575 ሚሊዮን ዶላር አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች መያዙን የኢስቶኒያ ፖሊስ አስታወቀ። የኢስቶኒያ ፖሊስ ከአሜሪካው የፌደራል መርምራ ቢሮ (ኤፍቢይ) ጋር በመተባበር ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ሲከታተል ቆይቶ ነው በቁጥጥር ስር የዋላቸው። የኢስቶኒያ ዜግነት ያላቸው የ37 ዓመት ጎልማሶቹ ሰርጌይ ፓታፔንኮ እና ኢቫን ቱሮጊን ተላለፈው እንዲሰጧቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚፈልጉ ተነግሯል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ፖሊቢየስ በተባለ የበይነ መ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9e1nv2lv8zo
health
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍ...
https://www.bbc.com/amharic/news-56066789
health
“ክትባት ቢገኝም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ”
የዓለም ጤና ድርጅት ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ አለ። የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል። ወረርሽኙ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። 32 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል። በአንዳንድ አገራት በሽታው እያገረሸ ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ውስጥ በአጠቃላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰው ታሟል። በሽታው ባገረሸባቸው የአውሮ...
https://www.bbc.com/amharic/news-54306899
business
የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር በኢኮኖሚው ላይ ምን ጫና ይዞ ይመጣል?
በአዲስ አበባ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ መስመር በሕገወጥ መንዛሪዎች የሚመራው የጥቁር ገበያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው ከ64 እስከ 68 ብር ድረስ በመመንዘር ላይ እንደሚገኝ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ይህ ዋጋ እስከ 72 ብር ድረስ ከፍ እንደሚል በዚሁ ሥራ ላይ ያለ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል። በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ አንድ ዶላር በ45 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ በጥቁር እና መደበኛ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ...
https://www.bbc.com/amharic/news-58089453
politics
ሳይፍ ጋዳፊ - የቀድሞው የሊቢያ መሪ ልጅ 'ፕሬዝደንታችሁ አርጋችሁ ምረጡኝ' እያሉ ነው
የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአማር አል-ጋዳፊ ልጅ በሚቀጥለው ወር በአገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ መመዝገቡ ተሰምቷል። ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በአንድ ወቅት ከአባቱ ሥልጣን ለመረከብ ጫፍ የደረሰ ሰው ነበር። ነገር ግን ከ10 ዓመት በፊት ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን በደል መደገፉ ስሙ እንዲጠለሽ አድርጎታል። ከዚህ ተቃውሞ በኋላ ሊቢያ ወደ ቀድሞ ሰላምና መረጋጋቷ መመለስ ፈጽሙ አልቻለችም። የመብት ተሟጋች ቡድኖች በሚወጥለው ወር የሚካሄደው ምርጫ ነፃና ፍትሐዊ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት አላ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59284872
business
በኢትዮጵያ ለወራት የቆየው የብድር እቀባ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ምን ውጤት ነበረው?
ላለፉት አራት ወራት ተግባራዊ ተደርጎ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ ሳምንት አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 20/2014 ዓ.ም ባንኮች የብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የብድር ክልከላው 'የምጣኔ ሀብትን አሻጥር' ለመከላከል በማለምና በጥቁር ገበያና በመደበኛ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ የተጣለው ባለፈው ነሐሴ ወር ነበር። ለመሆኑ ይህ ለወራ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59463389
sports
የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ
ትናንት ሌሊት በተከናወነው የዱባይ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ ቢቂላ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ የመጀመሪያ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ኦሊቃ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ 02፡06፡15 የፈጀበት ሲሆን፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሦስተኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኬኒያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ ነው። በሴቶች በተካሄደው ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ 02፡19፡37 ...
https://www.bbc.com/amharic/news-51232629
health
ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ ለድመት እና ውሾች የኮቪድ-19 ምርመራ ልታደርግ ነው
ደቡብ ኮሪያ በዋና ከተማዋ ሶል የሚገኙ ውሾች እና ድመቶች የኮቪድ-19 ምልክት ካሳዩ ምርመራ እንደሚደረግላቸው የሶል ሜትሮፖሊታን አስተዳደር አስታወቀ። የከተማዋ አስተዳደር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኮቪድ-19 የተያዘች ድመት መገኘቷን ተከትሎ ነው። ምልክቱን የሚያሳዩ የቤት እንሰሳት ብቻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም ቫይረሱ ለያዘው ሰው የተጋለጡና ትኩሳት ወይንም ደግሞ የመተንፈስ ችግር የገጠማቸው ድመትና ውሾች ምርመራ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል። ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55984271
health
ልጅን አቅፎ መተኛት ወይስ ለብቻ በተዘጋጀ አልጋ ላይ ማስተኛት?
ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህ ግን ከአገር አገር፣ ከባህል ባህል፣ ከኑሮ ደረጃ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊለያይ ይችላል። "ልጄ ክፍሉ ውስጥ ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በበርካታ የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለስ ሃሳብ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ይህ እየተለወጠ የመጣ ይመስላል። የህጻናት አስተዳደግና ሁኔታም እየተቀያየረ ነው። ይህ ደግሞ በምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለማችን ከፍል እየሆነ ያለ ነው። በአንዳንድ ባህሎች ከልጆች ጋር አንድ ክፍ...
https://www.bbc.com/amharic/news-56549405
health
በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል?
ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ...
https://www.bbc.com/amharic/news-54009884
health
ኮሮናቫይረስ፡ 'የኮቪድ-19 የመጀመሪያውን ዙር ክትባት መውሰድ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ያደርጋል'
የመጀመሪያውን ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት መወጋት የበሽታውን ሥርጭት በግማሽ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመለከተ። የፋይዘርና የአስትራዜኔካ የመጀመሪያው ዙር ክትባት የተሰጣቸውና ከሦስት ሳምንታት በኋላ በቫይረሱ እንዲያዙ የተደረጉ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፍ ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው ብሏ ጥናቱ። የዩናይትድ ኪንግድ ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የጥናቱን ውጤት "አስደናቂ ዜና" ሲሉ ገልፀውታል። ሚኒስትሩ ሰዎች የክትባት ተራቸው ከደረሰ ሳያመነቱ ሄደው እንዲከተቡም አሳስበዋል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉ...
https://www.bbc.com/amharic/news-56926149
sports
አርሰናል ቼልሲን አሸንፎ መሪነቱን ሲያስቀጥል ኒውካስል በግስጋሴው ቀጥሏል
ትናንት እና ከትናንት በሰቲያ የተከናወኑት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ባማረ ጨዋታ ታጅበው አስደናቂ ውጤቶች ተዘምግቦባቸው ተጠናቀዋል። አርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትትድ እና ሊቨርፑል ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን ይዘው ተመልሰዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በቪላ ፓርክ የበላይነት ተይዞበት 3 ለ 1 ሲሸነፍ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠረበት ጎል በክርስታል ፓላስ 2 ለ 1 ተሸንፏል። አርሰናል ትናንት በስታንፎርድ ብሪጅ ሄዶ ያገኘው ሦስት ነጥብ በትክክ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c723012gr2go
health
'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ ሕይወቱ አለፈ
በሰሜን ምሥራቅ አውስትራሊያ 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ አዛውንት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። እንደፖሊስ መረጃ ከሆነ ሟች እና የ36 ዓመቱ ተጠርጣሪ እግር የሚቆርጥበት ሁኔታን በተመለከተ አንዳች አይነት ስምምነትና 'ቅድመ ዝግጅት' ነበራቸው። የ66 ዓመቱን አዛውንት እግር በባትሪ ኃይል በሚሰራ መጋዝ ቆርጧል የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል። እንደ ፖሊስ ከሆነ ሁለቱ ግለሰቦች ቀድሞ የሚተዋወቁ ሲሆን፤ ሟቹ እግሩ በመጋዝ ...
https://www.bbc.com/amharic/news-60459117
sports
የአውሮፓ ታላላቅ አሰልጣኞች መልቀቅ እና ቀጣይ እጣ ፈንታቸው
አንቶኒዮ ኮንቴ ሴሪ አን ካሸነፈ በኋላ ኢንተር ሚላንን በቃኝ ብሏል። ዚኔዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ኃላፊነቱን ሲለቅ ቶተንሃም የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑን አለቃ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ለማስኮበልል እየሞከረ ነው። የሊግ 1 አሸናፊነት ክሪስቶፍ ጋልቲየርን በሊል ማቆየት አልቻለም። ጁቬንቱሶች አንድሪያ ፒርሎን በማሰናበት በማሲሚሊያኖ አሌግሪ ሊተኩት እየሠሩ ነው። በጀርመን ዮሃንስ ፍሊክ ከባየር ሙኒክ መነሳት ተመሳሳይ ውሳኔ በሌሎች ክለቦችም ዘንድ እንዲተገበር መንገድ ከፍቷል። የ2020 - 21 የውድድር ዘመን አቧራ...
https://www.bbc.com/amharic/news-57278702
politics
የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ሕግን አጸደቀ
የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በጦር መሣሪያ ቁጥጥር ላይ አዲስ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ይህ ሲሆን ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ወትሮም የዲሞክራቶችና የሪፐብሊካንን ጎራ የሚለየው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጉዳይ ከረዥም ዘመን ትግል በኋላ ነው ለዚህ የበቃው። 15 የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴዎች ረቂቁን ደግፈው ድምጽ ሰጥተዋል። ረቂቁ በ65 ድጋፍና በ33 ተቃውሞ አልፏል። ይህ የሆነው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተኩስ እሩምታን የከፈቱ ግለሰቦችን ተከትሎ በርካቶች ሕይወታ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c728rg65jkgo
business
የዋጋ ግሽበት እጅግ የሚያሰጋቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?
የዋጋ ግሽበት ዓለምን ከጥግ ጥግ አስግቷል። ከኢትዮጵያ እስከ ሲሪ ላንካ ከብራዚል እስከ ደቡብ አፍሪካ። ምግብ ተወዷል። ነዳጅ ተወዷል። ምን ያልተወደደ አለ? የተለይ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ መናር ዓለምን አስጨንቋል። በእርግጥ የዋጋ ግሽበት ከሌላው የዓለም ክፍል በላይ የሚያንገዳግዳቸው አገሮች አሉ። ለዚህ ምክንያቱ ሰብል አለመሰብሰቡ፣ ወረርሽኙ መክፋቱ እና የተፈጥሮ ጋዝ መጥፋቱ ነው። በዚህ ደግሞ በአፍሪካ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ዋነኛ ተጎጂ ናቸው። ቱርክ፣ ብራዚል እና ሲሪ ላንካም ይጠቀሳሉ። ከ...
https://www.bbc.com/amharic/news-60165449
business
ምጣኔ ሃብት ፡ አዲሶቹ የብር ኖቶች እና የያዟቸው የደኅንነት ገጽታዎች
ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። በቅርቡ ይፋ የተደረጉት የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ አጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸው የተገለጸ ቢሆንም ተጠቃሚዎች አንዳንድ ቅሬታዎች ሲያሰሙ ተደምጧል። በአዲሱ የ100 እና የ10 ብር ኖቶች ላይ ከላይ ወደ ታች የተዘረጋው መስመር ብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ እንደገለፀው በአንበሳው መካከል አያልፍም።...
https://www.bbc.com/amharic/54297291
business
ከባንክ አገልግሎት ወደ ተቆራረጠችው ትግራይ ገንዘብ ለመላክ የሚከፈለው ከባድ ዋጋ
ላለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየችው ትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ሕይወት ከባድ ሆኗል። በርካቶች ከጦርነቱ በፊት የነበራቸውን ሕይወት እና ጓደኝነት፣ ትምህርት እና ሥራ፣ ከምንም በላይ ሰላምን ይናፍቃሉ። የታመሙ ሮጥ ብለው የሚታከሙበት የሕክምና ተቋም ህንጻው ብቻ ቀርቷል። ሮጥ ብለው ያገኙትን የሚሸምቱበት ሱቅ ባዶውን ያዛጋል። ያለቻቸውን በውድ ዋጋ የሚሸጡ ነጋዴዎች ጋር ለመሄድ ደግሞ ገንዘብ ወሳኝ፤ ግን ከየት ይምጣ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ አብርሃ ይሕደጎ፣ በአንድ የ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/ce5g410x6j0o
politics
በምንጃር እና ፈንታሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው ምንድን ነው?
ከአዲስ አበባ ሰሜን ምሥራቅ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል በሚዋሰኑበት አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ነዋሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ገለጹ። የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሚዋሰኑበት አካባቢ ጥቃት መፈጸሙንም የሁለቱም ዞኖች አስተዳዳሪዎች ገልጸው በጥቃቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎችና በነዋሪዎች ላይ ሞትና ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ በግልጽ...
https://www.bbc.com/amharic/news-60930010
health
ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት
የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ...
https://www.bbc.com/amharic/57662274
business
ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ ግንባታውን ከጎበኙት የላሙ ወደብ ምን ይጠበቃል?
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የላሙ ወደብ ግንባታን ጎበኙ። መሪዎቹ በተጨማሪም ዛሬ ሐሙስ በሞምባሳ የተገኝተው ሊኮኒ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይን በይፋ ይመርቃሉ። 1.2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሞምባሳው ሊኮኒ ድልድይ ለቀጠናው የመጀመሪያው ሲሆን፤ ድልድዩ በ1.9 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወጪ የተገነባ ነው። ሁለቱ መሪዎች ትላንት በመርሳቤት ግዛት የተገነባውን የድንበር መተላለፊያ መርቀዋል። ከዚያም ወደ ላሙ ግዛት አቅንተው የወደብ ግንባታ ሂደቱን ቃኝተዋል። በጉብ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55255792
sports
'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራ ሊለቁ ነው
የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን ፆተኛ አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ሊለቁ ነው። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ "በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል" ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ይሁን እንጂ ሞሪ ጫናው በርትቶባቸው ሥልጣናቸውን...
https://www.bbc.com/amharic/56027725
health
በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ
በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። "ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪ...
https://www.bbc.com/amharic/news-54637492
health
የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮቪድ ምክንያት የተጣሉ ዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦችን ማንሳት ጀመሩ
ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ እና ጃፓንን ጨምሮ የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጎዞዎች ላይ ተጥለው የነበሩትን ክልካላዎች ማንሳት መጀመራቸውን ሬውተርስ ዘገበ። አገራቱ የዓለም አቀፍ በረራዎች መጀመር በቫይረሱ ስርጭት የተጎዳውን ምጣኔ ሃብታቸውን እንደሚያነቃቃው ታምኖበታል። እንደ እሲያ ፓሲፊክ አየር መንገደኞች ማህበር አሃዝ ከሆነ በእሲያ ብቻ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰኔ ወር ላይ የዓለም አቀፍ ተጓዦች ቁጥር 97 በመቶ ቀንሶ ነበር። አሁንም ቢሆን በርካታ የእሲያ አገራት ...
https://www.bbc.com/amharic/news-54506852
sports
ሴቶች 'ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራቸውን ለቀቁ
የቶክዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ “በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ነገር ግን ዛሬ አርብ ዕለት ለሰነዘርኩት ያልተገባ አስተያየ...
https://www.bbc.com/amharic/news-56038533
health
የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ
በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ "ማዕከል" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። "ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59165910
sports
አሜሪካ፡ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ቴኒስ ተጫዋቿ ኦሳካ ራሷን ከውድድር አገለለች
ጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናዮሚ ኦሳካ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ከታላቁ የኒው ዮርክ ቴኒስ ውድድር ራሷን አገለለች። “ጥቁር ሴት እንደመሆኔ እኔ ቴኒስ ስጫወት ከማየት በበለጠ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ አምናለሁ” ብላለች በትዊተር ገጿ። ምንም መሣሪያ ያልታጠቀው ጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ላይ ፖሊሶች ከጀርባው ተኩሰውበታል። እሁድ በኪኖሻ ግዛት ከተተኮሰበት በኋላ በመላው ዊስኮንሰን ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። በፖርትላንድ፣ ሚኒሶታና ሌሎችም ግዛቶች ተቃውሞው ቀጥሏል። ከ...
https://www.bbc.com/amharic/news-53929600
health
ረመዳን፡ ጾም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥና የሚሰጠው ጥቅም
ታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት እነሆ ተጀምሯል። በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት የሚተበቀው ይህ ወቅት ቀኑ በጾም ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በገጠማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ላይ ተሰብስቦ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን መካፈልና ከተለያዩ ሰዎች ጋር መሰባሰብ እንዲቀር ይመከራል። ስለዚህም በሐይማኖት አባቶች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ቅዱስ የጾም ወቅት እራሳችንንና ሌሎችን...
https://www.bbc.com/amharic/news-44128047
business
የኤሎን መስክ ኩባንያ የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ
ከአንድ ዓመት በፊት በክሪፕቶከረንሲ ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርጎ የነበረው የኤሎም መስክ ተቋም ቴስላ፤ ገዝቶት የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ። የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ከነበረው ቢትኮይን 75 በመቶ የሚሆነውን መሸጡ ተገልጿል። ቴስላ የሸጠው ቢትኮይን እአአ 2021 መጨረሻ ላይ 2 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ ነበር። ኩባንያው ዋጋው እየወደቀ ካለው የክሪፕቶካረንሲ ኢንቨስትመንት እራሱን እያራቀ ነው ተብሏል። የቢትኮይን ዋጋ በጥቂት ወራት ውስጥ 50 በመቶ በላይ ዋጋውን አጥቷል። ትልቅ ስም ካላቸ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cev51ryzz9xo
sports
የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው?
አፍሪካውያን ሯጮች በተለይም ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች በመካከለኛ እና በረጅም ርቀት የሩጫ መስኮች በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የበላይ ናቸው። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከዚህ በፊት በውድድሩ ውስጥ ያልነበሩ ስፖርቶችን በማካተት በዚህ ሳምንት መካሄድ ይጀምራል። በዚህም መሰረት አምስት የስፖርት አይነቶች በውድድሩ ውስጥ እንደተካተቱ ታውቋል፤ እነሱም የውሃ ላይ ሸርተቴ (ሰርፊንግ)፣ ተራራ መውጣት (ክላይምቢንግ)፣ ቤዝቦ...
https://www.bbc.com/amharic/news-57911750
business
የኬንያና የሶማሊያ እሰጥ አገባ የጫት ንግድን እየጎዳው ነው ተባለ
ኬንያ እና ሶማሊያ የገቡበት ዲፕሊማሲያዊ እስጥ አገባ በጫት ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተነገረ። የሶማሊያ መንግሥት ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ኬንያውያን ገበሬዎች ከፍተኛ ኪሰራ እየገጠማቸው መሆኑ ተግልጿል። ሶማሊያ ከወራት በፊት ከኬንያ በሚገባው የጫት ምርት ላይ እግድ የጣለችው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ነበር። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የኬንያ የጫት ምርት ወደ ሶማሊያ ከመግባቱ በፊት ኬንያ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባታል ትላለች ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55212239
politics
በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው
የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታወቁ። የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ እንደተናገሩት የወታደራዊ መሪው ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን እስላማዊ አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። መኮንኑ ጨምረውም ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም የአገሪቱ ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑ እና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል። አሁን ከሥ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9enzkkp0k8o
business
ቻይና የከፋ ድህነትን ከግዛቷ ማስወገዷን አወጀች
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸውን "በተዓምርዊ" ሁኔታ ከከፋ ድህነት መውጣቷን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት መቻሉን ገልፀዋል። ዢ ጂንፒንግ ቤይጂንግ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት "የተሟላ ድል" በማለት ስኬቱን አንቆለጳጵሰው "በታሪክ ውስጥ የሚመዘገብ" ብለውታል። ነገር ግን ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ያልተዋጠላቸው ባለሙያዎች ድህነት በቻይና እንዴት እንደተለካ ጠይቀዋል። በቻይና የከፋ ድህነት ተብሎ የሚ...
https://www.bbc.com/amharic/56201582
sports
የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለድሎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አመርቂ ድል ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመከተል የሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል። እነዚህም አራት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። በአሜሪካዋ ኦሪጎን ግዛት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘው የሜዳሊያ ብዛት በታሪክ የላቀ ውጤት...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2934kd1kw7o
sports
በሙስና ተፈርዶባቸው የነበሩት የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ አረፉ
የቀድሞ የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ ላሚን ዲያክ በ88 ዓመታቸው ሴኔጋል ውስጥ ማረፋቸው ተሰማ። ባለፈው ዓመት በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት ዲያክ ከአውሮፓውያኑ 1999 እስከ 2015 የዓለም አትሌቲክስ (የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር-አይኤኤፍ) ፕሬዝዳንት ነበሩ። በአውሮፓውያኑ 2020 ከሩሲያ አበረታች መድኃኒት ቅሌት ጋር ተያይዞ በሙስና እና በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአራት ዓመት እስራት እንዲቀጡ የበየነባቸው ሲሆን ሁለት ዓመቱ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59521751
politics
የትራምፕን የዋይት ሐውስ ሰነዶች መርማሪዎች እንዲመለከቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ
አንድ የአሜሪካ ዳኛ የካፒቶል አመጽን ከትትሎ ምርመራ የሚያደርገው የኮንግረስ ኮሚቴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዋይት ሐውስ ሰነዶችን እንዲመለከት ፈቃድ ሰጡ። ትራምፕ ሰዶቹን መርማሪ ኮሚቴው እንዳይመለከተው ያስችለኛል ያሉትን ሕጋዊ መብት አንስተው ተከራክረው ነበር። ምርመራውን የሚያካሂደው ኮሚቴ ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ መንግሥት ምክር ቤት ህንጻ (ካፒቶል ሂል) ላይ ባለፈው ዓመት ጥር ወር የተካሄደውን አመጽ ቀደመው ያውቁ ነበር የሚለውን ለመለየት ለሚያደርገው ጥረት መልስ ለማግኘት ነው። የአ...
https://www.bbc.com/amharic/news-59230353
sports
ጉዳፍ ጸጋይ በ5ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነች
በአሜሪካዋ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ባለቤት ሆናለች። ጉዳፍ በዚህ ድሏ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘቻቸውን የወርቅ ቁጥሮች አራት ማድረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በነበረበት ውድድር ጉዳፍ 14፡46: 29 በመግባት ነው ባለክብር የሆነችው። ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቺቤት ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ሌላኛው ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ለድሉ መሳካት ትልቅ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c1vg3ew6y76o
sports
ኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ የዓመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመረጠ
የማራቶኑ ጀግና ኤሉድ ኪፕቾጌ ቢቢሲ በሚያደርገው ምርጫ የአመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በማጠናቀቅ ታሪክ የሰራ የመጀመሪያው ሯጭ መሆን ችሏል። የ35 አመቱ ኬንያዊ በኦስትሪያዋ መዲና ቪየና በተደረገው የማራቶን ወይም የ42.2 ኪሎሜትር ርቀትን በ1 ሰዓት ከ 59 ደቂቃ ከ 40 ሰኮንዶች በመግባት አለምን አስደምሟል። • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች አጠናቀቀ • ኬኒያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰ...
https://www.bbc.com/amharic/news-50798738
health
ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር
የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። ...
https://www.bbc.com/amharic/news-53600806
business
የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ‘የማይቀመስ’ የሆነው ለምንድን ነው? ወደፊትስ ይቀንስ ይሆን?
በቅርቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ መዲና፣ ናይሮቢ የበረሩ ሦስት ተሳፋሪዎች በነፍስ ወከፍ 28 ሺህ ብር ከፍለናል ይላሉ። ሦስቱ ጓደኛሞች በአማካኝ 1፡45 ሰዓት ለሚወስደው የኢኮኖሚ ክፍል በረራ ደርሶ መልስ በድምሩ 84 ሺህ ብር ከፍለዋል። እርግጥ ነው የአውሮፕላን በረራ ዋጋ በተሳፋሪ የበረራ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ‘በኢኮኖሚ እና በቢዝነስ ክፍሎች’ ምርጫ ይለያያል። ቢሆንም በተለይ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ በአህጉረ አፍሪካ የአውሮፕላን በረራ አቅሙ ያላቸው የሚጓዙበት እየሆነ ነ...
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn41y4nn9jdo
politics
ተመድ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙት የማሊ ፐሬዚዳንት ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቀረበ
የማሊ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ባህ ንዳዋና ጠቅላይ ሚኒስተር ሞክታር ኦዋኔ በቁጥጥር ስር አዋለ መባሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ተልዕኮ መሪዎቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። ተልዕኮው በፈረንሳኛ ቋንቋ በትዊተር አማካኝነት ባቀረበው ጥሪ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ነገሮችን "እንድታረጋጋ"ም ጠይቋል። ይህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ የሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ጊዜያዊ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በዋና ከተማዋ አቅራቢያ በሚኝ ወታደራዊ ካምፕ መወ...
https://www.bbc.com/amharic/news-57237154
politics
የኢራንን የኑክሊየር ሳይንቲስቶች እያደነ የሚገድላቸው ማን ነው?
ባለፈው ሳምንት የእስራኤል ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ሰው ድንገት ተነስተው ወደ ቱርክ በረሩ። አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን የእስራኤል ቱሪስቶችን ለመግደል ተንቀሳቅሷል የሚል መረጃ ስለደረሳቸው ነው ፈጥነው ቱርክ የገቡት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስራኤልና ኢራን መካከል የጦፈ ግን ደግሞ ድብቅ ውጊያ እየተደረገ ነው፤ ከመጋረጃ በስተጀርባ። ይህ ነገር ወደለየለት ጦርነት እንዳያመራ መፈራቱ አልቀረም። ለበርካታ ዓመታት ሁለቱ አገራት በምሥጢራዊ ጥቃት ተጠምደው ነው የኖሩት። እስራኤል በምድር ላይ የኢራንን...
https://www.bbc.com/amharic/articles/c29xn1dj09zo
health
ኮሮናቫይረስ፡ የላቲን አሜሪካው ቁጥር-1 ቢሊዮነር በኮቪድ ተያዙ
በመላው ላቲን አሜሪካ የናጠጡ ሀብታም የሚባሉት ካርሎስ ስሊም በኮቪድ ተህዋሲ መያዛቸው ታወቀ፡፡ የ80 ዓመቱ ቢሊዮነር ካርሎስ ሜክሲኳዊ ሲሆኑ በቴሌኮሚኒኬሽን ቢዝነስ እውቅ ናቸው፡፡ ለጊዜው መጠነኛ የኮቪድ ምልክቶችን ብቻ እያሳዩ ነው ተብሏል፡፡ ልጃቸው በትዊተር ሰሌዳው እንደጻፈው ‹አባቴ ደህና ነው አታስቡ› ብሏል፡፡ የቢሊየነሩ በኮቪድ መያዝ ዜና የተሰማው የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የ67 ዓመቱ አንድሬስ ማኑል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሜክሲኮ ከዓለም አገራት ክፉኛ በኮቪድ ከተጎዱ አ...
https://www.bbc.com/amharic/news-55807195